Articles

  • የመጨረሻ ፍርድ ያገኙ ጉዳዮች /Res judicata/

    በመሠረቱ የፍትሐብሔር የክርክር አመራር ሥርዓት ዋነኛ ዓላማ የክርክሩን ሂደት ለማቀላጠፍና አንድ ደረጃ ላይ ሲደርስ መቋጫ ለማበጀት መሆኑ ይታወቃል። የፍትሐብሔርን ክርክር አንድ ደረጃ ላይ ሲደርስ እልባት እንዳይደረግበት በማቀድ ከተደነገጉት የፍትሐብሔር ሥነሥርዓት ጽንሰ ሐሳቦች አንዱ የመጨረሻ ፍርድ ያገኙ ጉዳዮች /Res judicata/ የሚለው ሲሆን ይህ ጽንሰ ሀሳብ በ1958ቱ የፍትሐ ብሔር ሥነ ስርዓት ሕጋችን ውስጥ በቁጥር 5 ድንጋጌ ስር በግልጽ ተቀምጦ እናገኘዋለን። በዚህ ድንጋጌ መሠረት የመጨረሻ ፍርድ ያገኙ ጉዳዮች ማለት በማናቸውም መልኩ በሕግ በተቋቋመ ፍ/ቤት ቀርበው የመጨረሻ ውሳኔ ያገኙ ጉዳዮችን የሚሸፍን መሆናቸውን በፍርድ፣ በብይን፣ በውሣኔ፣ በትእዛዝ፣ ወይም በጊዜያዊ አገልግሎት ባለው ትእዛዝ የመጨረሻ ውጤት አግኝተው በሌላ መልኩ ለመንቀሳቀስ የማይችሉ የክርክር ነጥቦችን ሁሉ የሚያጠቃልል ጉዳይ መሆኑን መገንዘብ የምንችለው ጉዳይ ነው። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/ 5 ሥር በተመለከተው አነጋገር አንድ ጉዳይ አስቀድሞ በፍርድ ያለቀ ነው ለማለት መረጋገጥ ካለባቸው ሁኔታዎች ውስጥ፦ ቀደም ሲል ቀጥተኛ የፍሬ ነገር ጭብጥ የነበሩ ጉዳዮች በድጋሚ በቀረበው ክስም ላይ በቀጥታ በፍሬ ነገር ጭብጥ ሆነው መቅረባቸው ፤ቀደም ሲል የነበረው ክርክር አሁን በክርክር ተሳታፊ በሆኑ ወገኖች ወይም ከእነሱ መብት በተላለፈላቸው ወይም ተላልፎላቸው በነበረ ወገኖች መሆኑንና እነዚህ ጉዳዮች ቀደም ሲል በተካሄደው ሙግት የመጨረሻ ፍርድ ያረፈባቸው መሆኑን ነው።

    ቀጥተኛ የፍሬ ነገር ጭብጥ በመጨረሻ ፍርድ መቃወሚያነት ሲቀርብ ተቀባይነት የሚኖረው ይኸው ጉዳይ በድጋሚ በቀረበው ክርክር ላይ መቅረቡ ሲረጋገጥ ነው። “ … ቀጥተኛ የፍሬ ነገር ጭብጥ …” የሚለው ሐረግ አጠቃላይ ይዘቱ ሲታይም በመጀመሪያው ክርክር ላይ ከአንደኛው ወገን ተጠይቆ በሌላኛው ወገን የተካደ ወይም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የታመነና በዚህ ላይ የፍርድ ውሣኔ ያረፈበት የክርክር ነጥብ ነው። በመሆኑም በድጋሚ በቀረበው ክስ በቀድሞው ክርክር ተሳታፊ በነበሩ ወገኖች ወይም ከእነሱ መብት በተላለፈላቸው ወገኖች በሚካሄድ መሆኑና በሁለተኛው ክስም የተያዘው የፍሬ ነገር ጭብጥ ከመጀመሪያው ጋር ተመሳሳይ ሆኖ የመጨረሻ ፍርድ ያረፈበት መሆኑ ከተረጋገጠ እንደሁም ጉዳዩ የመጨረሻ ፍርድ አርፎበታል የሚል ተቃውሞ በተከራካሪ ወገን ከተነሣ ተቀባይነት ያለው ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 5 እና 244(2) ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ነጥብ ነው።

    የሰ/መ/ቁ 62330 ቅጽ/12

  • የጉምሩክ ዋጋ ዝርዝር መግለጫ /Valuation DetailsDeclaration (VDD)/

    “Valuation Details Declaration
    (VDD)” means an electronic notification
    system where the declarant provides detailed
    statements and information, in addition to the
    goods declaration, to determine the customs
    duty and tax payable value of imported
    goods.

    “የጉምሩክ ዋጋ ዝርዝር መግለጫ /Valuation Details
    Declaration (VDD)/” ማለት ከዕቃ ዲክላራሲዮን
    በተጨማሪ የገቢ
    ዕቃዎችን የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ
    ማስከፈያ ዋጋ ለመተመን የሚያስፈልጉ
    መግለጫዎችና
    መረጃዎችን
    በዲክላራሲዮን አቅራቢው በዝርዝር
    ተሞልቶ ለኮሚሽኑ የሚቀርብበት
    የኤሌክሮኒክስ መረጃ ማሳወቂያ
    ሥርዓት ነው፡፡