ቢዝነስዎን ከሕግ ተጠያቂነት ይጠብቁ!
የንግድ ሕጎችን አለማክበር የገንዘብ ቅጣትን ብቻ ሳይሆን እስከ እስራት የሚደርስ ከባድ የወንጀል ተጠያቂነትን ሊያስከትል ይችላል።
ከባድ ጥፋቶች እና ቅጣቶች፦
- ያለፈቃድ መነገድ፡ ያለ ንግድ ፈቃድ መሥራት ከ10,000 እስከ 30,000 ብር በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እና ከ1 እስከ 3 ዓመት በሚደርስ እስራት ሊያስቀጣ ይችላል።
- የተሳሳተ መረጃ መስጠት፡ በምዝገባ ወቅት ሆነ ተብሎ የተሳሳተ መረጃ ማቅረብ አስተዳደራዊ እርምጃ እና የፈቃድ ስረዛ ያስከትላል።
- ሕገ-ወጥ ውድድር፦ የሌላውን ነጋዴ መለያ ስም መጠቀም ወይም ደንበኞችን የሚያሳስት መረጃ ማሰራጨት ተጠያቂ ያደርጋል።
ሕግን አክብሮ መሥራት ቢዝነስዎ በረጅም ጊዜ ስኬታማና ትርፋማ እንዲሆን ያደርጋል። ማንኛውም ጥርጣሬ ሲኖርዎ ወደ ሕግ ባለሙያ ወይም ወደ ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ቢሮ መሄድዎን አይርሱ።
Leave a Reply